የአዳሪ አብነት ት/ቤቱ የስኬት ምዕራፎች

Home|የአዳሪ አብነት ት/ቤቱ የስኬት ምዕራፎች

የአዳሪ አብነት ት/ቤቱ የስኬት ምዕራፎች

ከተመሠረተበት 2006 ዓ.ም ጀምሮ በ10 ተማሪዎች ሥራውን የጀመረው አዳሪ አብነት ት/ቤቱ አሁን ላይ በተለያየ ዕድሜና የትምህርት ደረጃ የሚገኙ ከ 150 በላይ ተማሪዎችን አቅፎ ይገኛል።

ለአብነት ትምህርት መስጫነት የሚያገለግሉ የቁጥር/ንባብ ፣ የዜማ ፣ የቅኔ ፣ የቅዳሴ ፣ የአቋቋም ፣ የትርጓሜ ፣ የስብከት ወንጌል እና የበገና ትምህርቶች የሚሰጡባቸው ስምንት (8) ጉባኤ ቤቶች በዘመናዊ መልክ ተገንብትዋል። እኚህም ጉባኤ ቤቶች፦

፩. የቁጥር እና ንባብ ጉባኤ ቤት

፪. የዜማ ጉባኤ ቤት

፫. የቅዳሴ ጉባኤ ቤት

፬. የቅኔ ጉባኤ ቤት

፭. የአቋቋም ጉባኤ ቤት

፮. የትርጓሜ ጉባኤ ቤት

፯. የስብከተ ወንጌል ጉባኤ ቤት

፰. የበገና ጉባኤ ቤት

 

በቤተክርስቲያኒቱ እና አዳሪ የአብነት ት/ቤቱ

ተማሪዎችን ከታች ጀምሮ በማብቃት ለቅኔ እና አቋቋም ጉባኤ ቤት መጀመር ትልቅ ሥራ ሠርቷል ።

ደቀመዛሙርት ባላቸው ጊዜ ከአብነት ትምህርቱ ጎን ለጎን የበና ድርደራን ተምረው ራሳቸውንና ሌሎችንም የማረጋጋት ጸጋ እንዲኖራቸው እንዲሁም በቅዱስ ዳዊት ሀብት ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ የበገና ሥልጠና በመውሰድ ላይ ናቸው ።

የአብነት ት/ቤቱ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርትን በማስተማር እስካሁን ድረስ ከ500 በላይ ተማሪዎችን የዲቁና ክህነት እና 15 ዲያቆናትን የቅስና ማዕረግ አስቀብሎ ወደ አገልግሎት አሰማርቷል።

የአብነት ት/ቤቱ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርትን በማስተማር እስካሁን ድረስ ከ500 በላይ ተማሪዎችን የዲቁና ክህነት እና 15 ዲያቆናትን የቅስና ማዕረግ አስቀብሎ ወደ አገልግሎት አሰማርቷል።