ለነገይቱ የቤተክርስቲያን ተስፋ የሆኑ ህፃናት እና ልጆችን በመንፈሳዊ ሕይወት በማሳደግ እና በማስተማር ትውልድን እንገነባለን!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
Welcome to Mezwer Debre Bisrat Saint Gabriel and Saint John the Baptist church and Abinet School.

ስለዚህ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ክብር እንደ ተቀበላችሁ እንዲሁ እርስ በርሳችሁ ተቀባበሉ። ሮሜ 15፡7
ብጹእ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሣልሳዊ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፤ የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል

ስለዚህ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ክብር እንደ ተቀበላችሁ እንዲሁ እርስ በርሳችሁ ተቀባበሉ። ሮሜ 15፡7

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥር ከሚገኙ የአብነት ትምህርት ቤቶች አንዱ የሆነው የመዝወር ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እና አዳሪ የአብነት ት/ቤት በጉራጌ ሃገረ ስብከት ፣ ምሁር አክሊል ወረዳ ፣ ከአዲስ አበባ በ212ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች.... ማንበቦትን ይቀጥሉ

ስለ ቤተክርስቲያኒቱ እና አዳሪ የአብነት ት/ቤቱ

በኵርን ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ ፤ በእስራኤል ልጆች መካከል በሰውና በእንስሳ ማኅፀን የሚከፍት በኵር የእኔ ነው ። ዘጸአት 13፡13

የመዝወር ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን የተመሠረተው የካቲት 30, 1993 ዓ.ም ሲሆን አዳሪ የአብነት ት/ቤቱ መስከረም 1 ቀን 2006 ዓ.ም ተመስርቷል። ደብሩ ከመመስረቱ በፊት በአካባቢው ያለው ምዕመን ቤተክርስቲያን ስላልነበረው ከሁለት ሰዓታት አድካሚ የሆነ ጉዞ በላይ በመሄድ ቤተክርስቲያን ይሳለም፣ የንግስ በዓላትን ያከብር፣ ስርዓተ ቤተክርስቲያንን ይፈጽምና ከዚህች ዓለም ወደዚያኛው ዓለም የሄዱትን የምእመናን ሥጋ ያሳርፍ ነበር፡፡

የአብነት ት/ቤቱ ርዕሰ መምህር የሆኑት መልአከ ብርሃን ቆሞስ አባ ኢያሱ ሰብስቤ ።

የቤተክርስቲያኒቱ እና አዳሪ የአብነት ት/ቤቱ ተልእኮ

  • ለቤተክርስቲያኒቱ የሚሰጡ የበኩራት ልጆችን ከሶስት ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ተቀብሎ በመንፈሳዊ ሕይወት በማሳደግ እና የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት ማለትም የአብነት ትምህርትን ፣ ወንጌልን ከዘመናዊ ትምህርት ጋር አስተምሮ ለቤተክርስቲያን የተመረጡና የተቀደሱ አገልጋዮችን ማፍራት፣
  • ከአራቱም የሀገሪቱ ክፍል (ከሰሜን ፣ ከደቡብ ፣ ከምስራቅ ፣ ከምዕራብ ኢትዮጵያ) የሚመጡ ተማሪዎችን ያለልዩነት ተቀብሎ በማስተማር የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን (መምህራን፣ ካህናት ፣ ዲያቆናት) እጥረት መቅረፍ፣
  • ጥራት ያላቸው በዕውቀት ብቻ ሳይሆን በወንጌል የሥነምግባር እሴት የጎለበቱ ለቤተክርስቲያን መድኃኒትና ዕረፍት እንጂ ችግር ፈጣሪ ያልሆኑ ካህናት ፣ ዲያቆናት ፣ መምህራን አገልጋዮችን ማፍራት፣
  • በልዩ ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ በአገልጋይ እጥረት የምትሰቃየውን በገጠሩ የሃገራችን ክፍል ያለችውን ቤተክርስቲያን የአገልጋዮቿን ቁጥር መጨመር ነው።
ዘጋቢ ፊልም

ቤተክርስቲያንያኒቱ እና የአዳሪ የአብነት ት/ቤት ዘጋቢ ፊልም

አብነት ት/ቤቱ ለቤተክርስቲያን የሚሰጡ የበኩራት (የመጀመሪያ ልጆችን) እንዲሁም ከአራቱም የሀገሪቱ ክፍል የሚመጡ የአብነት ተማሪዎችን ያለልዩነት ተቀብሎ የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት ማለትም የአብነት ትምህርትን ፣ ወንጌልን በማስተማር የተመረጡና የተቀደሱ አገልጋይ መምህራንን ፣ ካህናትን እና ዲያቆናትን የማፍራት ዓለማ ያለው ነው።

የገዳሙ የልማት እንቅስቃሴዎች

በደብሩ የሚደርሱ የዘወትር ስብሐተ እግዚአብሔር