Misson
የቤተክርስቲያኒቱ እና አዳሪ የአብነት ት/ቤቱ ተልእኮ
- ለቤተክርስቲያኒቱ የሚሰጡ የበኩራት ልጆችን ከሶስት ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ተቀብሎ በመንፈሳዊ ሕይወት በማሳደግ እና የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት ማለትም የአብነት ትምህርትን ፣ ወንጌልን ከዘመናዊ ትምህርት ጋር አስተምሮ ለቤተክርስቲያን የተመረጡና የተቀደሱ አገልጋዮችን ማፍራት፣
- የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን በአውደ ምህረት ፤ በኮርስ እና በርህቀት ለምዕመናን ማድረስ ።
- ከአራቱም የሀገሪቱ ክፍል (ከሰሜን ፣ ከደቡብ ፣ ከምስራቅ ፣ ከምዕራብ ኢትዮጵያ) የሚመጡ ተማሪዎችን ያለልዩነት ተቀብሎ በማስተማር የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን እጥረት መቅረፍ፣
- ጥራት ያላቸው በዕውቀት ብቻ ሳይሆን በወንጌል የሥነምግባር እሴት የጎለበቱ ለቤተክርስቲያን መድኃኒትና ዕረፍት እንጂ ችግር ፈጣሪ ያልሆኑ መነኮሳት ፤ ካህናት ፣ ዲያቆናት ፣ መምህራን አገልጋዮችን ማፍራት፣
5. በልዩ ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ በአገልጋይ እጥረት የምትሰቃየውን በገጠሩ የሃገራችን ክፍል ያለችውን ቤተክርስቲያን የአገልጋዮቿን ቁጥር መጨመር ነው።
6. በአካል እየተሰጠ ያለውን የአብነት ትምህርት በቀጥታ ስርጭት ወይም በ Online ለሚፈልጉ ምዕመናን ማዳረስ ።
7. ደቀመዛሙርቱን ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የሥራ ፍቅርና ልምድ እንዲኖራቸው በገዳማዊ ልማት ሥራ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማስቻል ።
ምስረታ እና ሂደት
ከተመሠረተበት 2006 ዓ.ም በ10 ተማሪዎች ሥራውን የጀመረው አዳሪ አብነት ት/ቤቱ አሁን ላይ በተለያየ ዕድሜና የትምህርት ደረጃ የሚገኙ ከ 120 በላይ ተማሪዎችን አቅፎ ይገኛል። የአብነት ት/ቤቱ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርትን በማስተማር እስካሁን ድረስ ከ300 በላይ ተማሪዎችን የዲቁና ክህነት እና 15 ዲያቆናትን የቅስና ማዕረግ አስቀብሎ ወደ አገልግሎት አሰማርቷል።

የዚህ ድህረ ገጽ ዋና አላማው
በመዝወር የሚከናወኑ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ሁሉ ለዓለም ማስተዋወቅ
ለ. የሥርዓተ አምልኮቱ አገልግሎት
—-ጸሎቱ
—-ስብከተ ወንጌሉ
ሐ. የሰበካ ጉባኤው እንቅስቃሴ
ልዩ ልዩ ሥልጠናዎችን፣የኦን ላይን እና የርህቀት ትምህርቶችን ለዓለም ማዳረስ።
መ. የልማት ሥራ እንቅስቃሴ
—-ግብርናን የተመለከተ
——ግንባታን በተመለከተ
ሠ. የደብሩ ዓላማ፣ራዕይ እና ግቡ
የቤተክርስቲያንን ሥርዓት፣ዶግማ እና ቀኖና ሳይጋፋ ሥልጣኔን ለገቢ ምንጭነት መጠቀም
ዋና ተኩረት
ለቤተክርስቲያኒቱ የሚሰጡ የበኩራት ልጆችን ከሶስት ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ተቀብሎ በመንፈሳዊ ሕይወት በማሳደግ እና የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት ማለትም የአብነት ትምህርትን ፣ ወንጌልን ከዘመናዊ ትምህርት ጋር አስተምሮ ለቤተክርስቲያን የተመረጡና የተቀደሱ አገልጋዮችን ማፍራት
